Friday, September 1, 2017

#አሳዛኝ ዜና ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያኖች የሚለውን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወገደ። ,,,,,,,በእግዚአብሄር ስም share,,,,,,በማድረግ ለወገኖቻችን አዳርሱ ይጠነቀቁ ዘንድ!!!!!!!



Image may contain: text

- “ኢትዮጵያ” የሚለውን ቃል ከምዕራፎቹ ውስጥ ያስወገደው አዲስ የመጽሃፍ ቅዱስ ህትመት ጉዳይ
በቅርቡ በጀርመን ኢቫንጀሊካል ቤተክርስቲያን የተዘጋጀ መጽሃፍ ቅዱስ ቀድሞ ከ40 በላይ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን ‹‹ኢትዮጵያ›› እና ‹‹ኢትዮጵያኖች›› ሚለውን ቃል በማስወገድ በአዲስ ቃል ተክቶታል፡
ለምሳሌ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚያብሔር ትዘረጋለች የሚለውን ኩሽ እጆቿን ወደ እግዚያብሔር ትዘረጋለች ብለውታል።
...............
ከሰሞኑ ከወደ ጀርመን አንዱ የኦነግ ርዕዮተ አለም ተጋሪ «አማራ ጫነብን» ፤«ሃይማኖታችን ዋቄ ፈና እንጂ ክርስትናን አማራ የጫነብን ሃይማኖት ነው» በማለት ኦነግ በፕሮግራም ሲታገለው የኖረውን ክርስትናን እንዳዲስ ጽፎ ለኢትዮጵያና ለአለም ለማስተማር መነሳቱን ነግሮናል። ይገርማል። ሬቨረንድ ነኝ የሚለው በንቲ ቴሶ ከኦነግ የነፍስ አባት ከጀርመን በተማረው ኢትዮጵያን የማጥፋት ትምህርት ታግዞ «ከጳጳሱ ቆሱ» እንዲሉ ክርስትናን ለኢትዮጵያና ለአለም ኢትዮጵያ የሚለውን የአገር መጠሪያ ደምስሶ እንደ አዲስ በጻፈው የበንቲ ቅጂ [Rev. Benti's version] መጽሐፍ ቅዱስ ሊያስተምር እንደሆነ በድፍረት ደስኩሯል።
ሬቨረንድ በንቲ ቴሶ ኢትዮጵያ ለኛ ስድብ ነው ያለበት ምክንያት አንዳንዶች እንደሚሉት «ኢትዮጵያ» የሚለው ቃል ከግሪኮች የተወረሰ እንደሆነ ይናገሩና «ኢቶስ» ዋዕይ [ሙቀት] «ኦፕ» «ሲስ» ገጽ፣ አርአያ ማለት እንደሆነና እነዚህን ሁለቱ ቃላት በማጣመር «ኢቲኦፕያ» ወይም «ኢቲኦፕስ» የሚል ይሰጣል፤ ይህም ማለት «የተቃጠለ ፊት ማለት ነው» የሚለው ትርክት ይዞ ነው።
ሬቨረንድ በንቲ በግሪክኛ የሰጠው ፍቺ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ስያሜ እንዳልሆነ እሱ «የተቃጠለ ፊት ማለት ነው» የሚል ትርጉም ይሰጣል ለማለት የጠቀሰው ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው ባለቅኔና ገጣሚ ሆሜር በመጽሐፉ ኢትዮጵያ ያለው ጥቁሩን ብቻ ሳይሆን ቀዩንም ኢትዮጵያ ብሎት ይገኛል። በሌላ አነጋገር በታላቁ ግሪካዊ ኦሜር ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ብቻ ሳይሆን ቀይ፤የቀይ ዳማ ቀለም ያለው ሕዝብ ማለት ነው እንደሆነ ኢትዮጵያን ከገለጸበት ዶሴው መገንዘብ ይቻላል።
በሌላ አነጋገር «ኢትዮጵያ» የሚለውን ቃል የግሪክ ፍቺ ሰጥቶ «ለኛ ስድብ ነው» ሬቨረድን በንቲ ቴሶ ስድብ ነው ያለውን፤በግሪክ አፉን የፈታው ባለቅኔው ሆሜር ግን ስ ለኢትዮጵያ ሲናገር ኢትዮጵያውያን በጉልበት ኃያላን፤ በውበት የተደነቁ፤ የዋሆች፤ በጠባይ ጭምቶች፤ ትህትናን ፍቅርን የተመሉ ናቸው ሲል በአክብሮት ይገልጻቸዋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ በግሪክ ሬቨረድን በንቲ ቴሶ እንደሚለው ስድብ ቢሆን ኖሮ ግሪክኛ ተናጋሪው ሆሜር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን እጅግኑን አድንቆና ከፍ አድርጉ አይጠራቸውም ነበር። ስለዚህ ሬቨረንድ በንቲ ቴሶ ኢትዮጵያ የሚለው የቦታ ስም የግሪክ ቃልና ስድብ ነው ያለው መሰረት የሌለውና ከሀቅ የራቀ መሆኑን ከሆሜር መረዳት እንችላለን።
አምርረው የሚጠሉትን ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከመጽሕፍ ቅዱስ ለመደምሰስ የተነሱት እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች አገር በቀል ወኪሎች ነገም ተነስተው በቅዱስ ቁርዓን ተጠቅሶ የሚገኘውንም «ኢትዮጵያ» የሚለውን የአገር ስም ይቀየር ብለው ዘመቻ እንደማይጀምሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ስለዚህ ምንም እንኳ ማህበራዊ ሚዲያውን በሕዝባችን ባጠቃላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማሳወቅና ያ ትውልድ ያጠፋውን ታሪካችንን እንድናውቅ ለማድረግ ብንጠቀምበትም የአገር ተቆርቋሪና የሚያዝን የሃይማኖት አባት ስለሌለን ታሪካችና ባለም ላይ ኢትዮጵያ በክርስትናም በእስልምናም ያሳረፈችው አሻራ ሲደለዝ ዝም ብለን ልናይ አንችልምና ጸጋዬ ገብረ መድህን እንዳለው «እንናገራለን እውነት»።
ኦቶማን ቱርክና ግብጽ አስራ ሁለት ጊዜ፣መዲስቶች ሶስት ጊዜ፣ ጥሊያን ሁለት ጊዜ፣ እንግሊዝ አንድ ጊዜ ሞክረው ውርደት ተከናንበው ሽንፈት ቢጋቱም በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን ቁርሾና ቂም ግን የኢትዮጵያ ጠላቶች አገር በቀል ወኪል በሆነው በአሁኑ መንግስት በኩል እየተወጡ ናቸው። ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ጠላቶች በኢትዮጵያ ላይ በቀጥታ ሞክረውት ያልተሳካላቸውን ፕሮግራም በጠላቶቻችን ድጋፍ ለስልጣን በበቃው በኩል ያልተፈጸላቸው አንዳች ነገር የለም። የዘመኑ ርዕዮተ ዓለም ተጋሪዎች በክርስትና ስም ተሸፍነው «ኢትዮጵያ» የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲደመሰስ ስለተነሱ ስለክርስትናና ኢትዮጵያ ታሪክ ግንኙነት የምናውቀውን ነገር ልንናገር ተገደናል። ነገም ሌላ ቀን ነውና የማይተኙልን ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ከቅዱስ ቁርዓን ለማለያየት ሲመጡብንም ዝም አንልምና ያኔ ቀኑ ሲደርስ እንደዛሬው ሁሉ በቅዱሳን ሀይማኖቶችና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት የምናውቀውን እውነት እንናገራለን።
 @@@@አቋም!
ስለክርስትናና እየሱስ ክርስቶስ እኛ ኢትዮጵያውያን በደማምን ዓለምን እናስተምራለን እንጂ ከኛ ከሺ አመታት በኋላ ክርስትናን የተቀበለው አለም ሊያስተምረን አይችልም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ስለ ክርስትና የምናውቀው በስሚ ስሚ ወይንም ሰባኪ ነግሮን ሳይሆን «ከፈረሱ አፍ» እንደሚባለው ስለክርስትና የምናውቀው የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ክርስቶስ አለምን እንዲያስተምሩ ካሰማራቸው መካከል ከሆነው ከኃዋርያው ከፊሊጶስ ነውና። ታሪኩ ባጭሩ እንዲህ ነው።
የኃዋርያት ስራ ምዕራፍ ስምንትን ያነበበ ሁሉ እንደሚገነዘበው እየሱስ ክርስቶስ ሞቶ በተነሳ በአመቱ በ34 ዓ.ም. ኃዋርያት አለምን ለማስተማር ሲበተኑ ኃዋርዋው ፊሊጶስ በጋዛ አቅጣጫ አድርጎ ሲሄድ በሰረገላ ላይ ተቀምጦ ወደ እየሩሳሌም ሊሳለም በመሄድ ላይ የነበረውን ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ የንግስት ህንደኬን አቃቤ ንዋይ የኢሳያስን መጽሐፍ [ትንቢት] ሲያነብ አግኝቶት የትንቢቱን ፍቺ ካስረዳው በኋላ አዲሱን ሃይማኖት ለመከተል «እመንና ተጠመቅ» ባለው መሰረት ወደ ወንዝ ወርደው ጃንደረባው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃዋርዋያ በፊሊጶስ ተጠምቆ ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።
ልብ በሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃዋርያ የሆነው ፊሊጶስ ጃንደረባውን ሲያጠምቅ የተጠመቀው አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባው ብቻ አይደለም። ምክንያቱም የንግስቲቷ ልዑክ መሪና የኃብቷ ኃላፊ ወደ እየሩሳሌም በሰረገላ ሲሄድ ብቻውን አይሄድም። ይህ ማለት ጃንደረባው ወደ እየሩሳሌም በሰረገላ ሲሄድ ብዙ አጃቢና ጋሻጃግሬ አብሮት ይኖራል ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ «እንደንጉሱ አጎንብሱ» በሚባልበት ዘመን ደግሞ የልዑኩ መሪ ጃንደረባው ሲጠመቅ ልዑኩ ባጠቃላይ ይጠመቃል ማለት ነው።
እነዚህ ከአለም አስቀድመው ክርስትናን የተቀበሉት ኢትዮጵያዊው ጃንደረባና ወደ እየሩሳሌም አብረውት ሄደው የተጠመቁት የልዑክ ቡድኑ አባላት ከእየሩሳሌም ጉብኝት በኋላ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ጃንደረባው ዘመዶቹንና በስሩ ያለውን ሕዝብ፤ ባለሟሎቹም ዘመዶቻቸውንና ተከታዮቻቸውን ሁሉ እንዲጠመቁ ያደርጋሉ ወይንም ያስተምራሉ። ይህ ማለት ባጭሩ ክርስትና ኢዛና የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባ ሃይማኖት አይደለም ማለት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትና ታሪክ የኢዛናን ዘመን ለየት የሚያደርገው ክርስትና የመንግሥት ሃይማኖት መሆኑ ብቻ ነው እንጂ ኢዛና የመጀመሪያው ክርስቲያን ንጉስ ከመሆናቸው ከሶስት መቶ አመት በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ [ሙሉ በሙሉ ባይሆንም] ክርስቲያን የነበረና ክርስትናን የሚያስተምሩ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖቱ መምህራን ነበሩ ማለት ነው።
የጀርመኑ ፓስተር በንቲ ቴሶ ክርስትናን የተማረባት አገር ጀርመን ክርስትናን የተማረችው ሲልቲክ የሚባሉ ሕዝቦች የሚኖሩበትን የምዕራቡን የጀርመን ክፍል የግዛቷ አካል አድርጋ ታስተዳደር ከነበረችው ከሮማን ኢምፓየር ነው። ኢትዮጵያውያን ክርስትናን ተቀብለው ላልተጠመቀው ኢትዮጵያዊና ለቀሪው አለም ክርስትናን በሚያስተምሩበት ወቅት የሮም ቄሳሮች በክርስትናና በክርስቲያኑ ላይ ሲቀልዱ ነበር። ከዚህም አልፎ የሮማ ቆሳሮች የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያዎች የሆኑትን ጴጥሮስና ጳውሎስን በአደባባይ ሰቅለዋቸዋል። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በአለም ላይ ከክርስትና ቀደምት አስረማሪዎች የምንመደብ ነን እንጂ የክርስቶስ ኃዋርያት የሆኑትን ጴጥሮስና ጳውሎስን የሰቀሉ ቄሳሮች ክርስትናን ካስተማሯቸው የክርስትና ተማሪዎች ክርስትናን አንማርም።
ከዚህ በተጨማሪ በአለም ላይ ካሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ሁሉ እጅግ ጥንታዊውና የተሟላው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው በግዕዝ ፊደል የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኝው የግዕዝ መጽሕፍ ቅዱስ እውነትም ጥንታዊና በአለም ላይ ከሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ሁሉ የተሟላ እንደሆነ የበንቲ ቴሶ መምህራን አውሮፓውያን ሳይቀሩ አረጋግጠናል ብለው ነግረውናል። በዚህ ጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በደማቅ ቀለም ሰፍሮ የሚገኘውን «ኢትዮጵያ» የሚለውን ቃል በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተሰናዳው የእንግሊዙ ንጉስ የንጉስ ጀምስ መጽሕፍ ቅዱስ ቅጂ [King James Version] «ኩሽ» ብሎ ሊለውጠው የሚችልበት የሞራል ልዕልና የለውም። ምን ይሄ ብቻ! አይደለም ከንጉስ ጀምስ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስትናን የተማረው ፓስተር በንቲ፤ ፓስተር በንቲ የተማረበትን መጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ [King James Version] እንዲዘጋጅ ያደረገው የእንግሊዙ ንጉስ ጀምስ ራሱ ክርስትናን ከኢትዮጵያ ይማር እንደሆነ እንጂ ለኢትዮጵያ ክርስትናን ሊያስተምራት አይችልም።
እንግሊዞች ኢትዮጵያን አቢሲኒያ ይሏት ነበር። አውሮፓውያን የሆኑት ግሪኮች ደግሞ የቅድመ ክርስቶስ ልደት በፊት ኢትዮጵያን ኩሽ ይሏታል። ከነዚህ አገራት ሁሉ ግን ቀድመው ኢትዮጵያውያን ክርስትናን ተቀብለዋል። የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስም በነዚህ አገራት ቋንቋዎች ከተጻፈው በጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ እጅጉን ጥንታዊ ነው። ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላሉት የቦታ ስሞች ማመሳከሪያ ሊሆን የሚችለው ቀድሞ የነበረውና ጥንታዊ የሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ኦነጋውያን ግን የእውቀት ጾመኞችና በኢትዮጵያ ጥላቻ የናወዙ ስለሆነ የሚፈልጉትን ታሪክ ለመጻፍ አለም የተቀበለውን ጥንታዊውንና ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው የግዕዝ መጽሕፍ ቅዱስ ማውገዝ እንጂ ለማመሳከሪያ መጥቀስ አይፈልጉም። ከሰሞኑ እነ በንቲ ቴሶ ያደረጉት ይህንን ነው።
ለማንኛምው በአለም ላይ ክርስትናን ከተቀበሉት በመጀመሪያው ረድፍ የምትገኘዋ ኢትዮጵያ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃዋርያ ተጠምቀው ክርስትናን ለአለም ያስተማሩት አበው እያሏት የክርስቶስ ኃዋርያት የሆኑትን ጴጥሮስና ጳውሎስን የሰቀሉ ቄሳሮች ክርስትናን ያስተማሯቸው የክርስትና ተማሪዎች ካስተማሯቸው የጀርመን ተማሪዎች ከሆኑት ከነፓስተር በንቲ በRev. Benti version of the "bible" ክርስትናን ልትማር አትችልም። 

No comments:

Post a Comment